ከክፉ መናፍስት መጠበቅ

ከክፉ መናፍስት መጠበቅ

ማጠቃለያ

ርኩሳን መናፍስት ኃይል ያላቸው ቢሆንም፤ ሆኖም ግን የመሲሑን የሱስ ያህል ኃያል አይደሉም፡፡ ይህ በራሪ ጽሑፍ የሱስ እንዴት በሥቃይ ውስጥ ከነበሩ ሰዎች አጋንንትን እንዳስወጣና ፈውስ እንዲያገኙ እንደረዳ ይገልጻል፡፡ እርሱ ዛሬ ለእኛም ተመሳሳይ ነገር ሊያደርግልን ይችላል፡፡ የእርሱ መጽሐፍ ከማንኛውም አጋንንታዊ ትንኮሳ እና ጭቆና ነጻ ለመሆን ማወቅ ያለብንን ነገር ሁሉ ያስተምረናል፡፡ በተጨማሪ እርሱ ዳግም ከመመለሱ በፊት ከሚከሰቱ ከአጋንንታዊ አስመሳዮች መታለል ራሳችን እንዴት እንደምንጠብቅ ይኸው መጽሐፍ ያስተምረናል፡፡

አውርድ

ጂኒዎች በሁሉም ሥፍራ አሉ:: መናፍስት፣ አጋንንት ወይም ጂኒ በሚል ስያሜ ቢጠሩም፣ አስፈሪ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ መናፍስት ጠሪዎች፣ ጠንቋዮችና ደብተራዎች በአንዳንድ ማኅበረሰብ መሀል ከፍ ያለ ዝና ቢኖራቸውም፣ ከክፉ ሊጠብቁዎ እንደሚችሉ እርግጠኛ መሆን ይቻላል?

ከርኩሳን መናፍስት እንዴት መጠበቅ እንደሚቻል ሦስት ቀለል ያሉ ቅደም ተከተሎችን ላካፍሎት እወዳለሁ፡፡ ከዚያም መናፍስቱን መፍራት እንደማይኖርቦት ያስተውላሉ፡፡

ከርኩሳን መናፍስት መጠበቅ፤

ሰውየው እርቃኑን ከመሆኑም በተጨማሪ ያለማቋረጥ ድምጹን ከፍ አድርጎ ይጮኽ ነበር፡፡ በብዙ ጂኒዎች በመያዙ ማንም ሊረዳው አልቻለም፡፡ የመንደሩ ሰዎች በሰንሰለት ሊያስሩት ሞክረዋል፣ ነገር ግን ከሰው አቅም በላይ በሆነ ኃይል ሰንሰለቱን ይበጣጥሰውና ወደ ሚኖርበት መቃብር ቦታ ይገሠግሳል፡፡ ቀኑን አምርሮ እየጮኸና ሰውነቱን በድንጋይ እየቆራረጠ ያሳልፍ ነበር፡፡

ኢሳ አል መሲህ በመባል የሚታወቀው የሱስ ክርስቶስ ወደዚያ ስፍራ እስኪደርስ ድረስ ሁኔታው በዚህ መልኩ ቀጠለ፡፡

ሰውየው እጅግ ከመሠቃየቱ የተነሣ እርዳታ ለመጠየቅ ገና አፉን ሲከፍት፣ ይተወው ዘንድ ጂኒው በየሱስ ክርስቶስ ላይ ጮኸበት፡፡ ሆኖም የሱስ ሰውየውን ትቶት አልሄደም፡፡ ምክንያቱም እየሆነ የነበረውን በሚገባ ያውቅ ነበር፡፡ ስለዚህ ጂኒው ሰውየውን ለቅቆ ይወጣ ዘንድ በድፍረት አዘዘው፡፡

ጂኒውም፡ “ከአገር እንዳያስወጣቸው አጥብቆ ለመነው፡፡” ርኩሳን መናፍስቱም በአቅራቢያው ወደ ተሰማሩ ዐሣማዎች ውስጥ እንዲገቡ ይፈቅድላቸው ዘንድ ጠየቁት፡ የሱስም ሰውየውን ለቀው ንጹህ ወዳልሆኑት እንስሳት እንዲገቡ አዘዛቸው፡፡ ወዲያውኑ ሰውየው ወደ አዕምሮው የተመለሰ ሲሆን፣ የዐሣማው መንጋ በገደሉ አፋፍ በመንደርደር ቁልቁል ወርደው በባሕር ውስጥ ሰጠሙ፡፡

በመጨረሻ ሰውየው ነጻ ሆነ፡፡ ለተደረገለትም አብልጦ አመሰገነ! ይህ ግን ብቸኛው ታሪክ አይደለም፡፡ የሱስ ክርስቶስ በርኩሳን መናፍስት ላይ ከፍተኛ ኃይል ነበረው፡፡ በሄደበት ሥፍራ ሁሉ በጂኒ የተያዙ ሰዎችን ነጻ ያወጣ ነበር፡፡ ለተከታዮቹም በዲያብሎስ ላይ ሥልጣን ሰጣቸው:-

“እንግዲህ. . . በጠላትም ኃይል ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቻችኋለሁ፤ የሚጎዳችሁም አንዳች ነገር አይኖርም፡፡ ይሁን እንጂ መናፍስት ስለተገዙላችሁ በዚያ ደስ አይበላችሁ፤ ስማችሁ ግን በሰማይ ስለ ተጻፈ ደስ ይበላችሁ፡፡” (ኢንጂል በመባልም ከሚታወቀው የወንጌል መልእክት፡ ሉቃስ፡ 10፡19–20)፡፡

የሱስ ክርስቶስን ስንከተል፣ በዚህ ሕይወት ደኅንነት፣ ለሚመጣው ሕይወት ደግሞ ማረጋገጫ እናገኛለን! ከርኩሳን መናፍስት ነጻነት ማግኘት የሚያስችሉንን ሦስት ቅደም ተከተሎች እንመልከት፡

ቅደም ተከተል 1:--የየሱስ ክርስቶስን የስሙን ኃይል አጽንተው ይያዙ፣

ቀዳሚው አካሄድ በየሱስ ክርስቶስ ስም የእግዚአብሔርን ጥበቃ መሻት ነው፡፡ እኛ በራሳችን፣ አቅመ ቢሶች ነን፡፡ ነገር ግን የየሱስ ክርስቶስን ስም በሕይወታችን አጽንተን ስንይዝ ርኩሳን መናፍስት አቅመ ቢሶች ይሆናሉ!  የሱስ ስለ ተከታዮቹ እንዲህ ብሎአል:- “በስሜ አጋንንትን ያወጣሉ” (የማርቆስ ወንጌል፡ 16:17)፡፡

የሱስ ክርስቶስ ነጻ እንደሚያወጣዎ በሙሉ ልብዎ ቢያምኑ፣ እርሱ ያደርገዋል! ይህንን ልመና ወደ እግዚአብሔር ያቅርቡ፡ “ጌታ ሆይ፣ በላክኸው በየሱስ ክርስቶስ ስም እባክህን ከርኩስ መናፍስት ነጻ አውጣኝ!”

ቅደም ተከተል 2:--ለውስጥ እና ለውጭ ንጽህና መሻት ይኑርዎ፤

ዲያብሎስ መረጋገጫ የሚያገኝበት ምንም ዓይነት ክፍተት እንዳንሰጠው የሱስ ክርስቶስ አስተምሯል፡፡ “የዚህ ዓለም ገዥ ስለሚመጣ. . . . እርሱም በእኔ ላይ ሥልጣን የለውም፡፡” (የዮሐንስ ወንጌል 14፡30)፡፡ እኛም ሕይወታችንን ከማንኛውም የርኩስ ተጽእኖዎች ማጽዳት ይኖርብናል፡፡

ዲያብሎስ “በእኛ ላይ አንዳችም ነገር የለውም” ማለት ምን ማለት ነው? በልባችን ወይም በቤታችን ውስጥ የእርሱ የሆነ ምንም ነገር የለም ማለት ነው፡፡ መናፍስት መለማመኛ ኪታቦችን ከእኛ አርቀን መጣል አለብን፡፡ ኃጢአት ከሚሆኑ የወሲብ ትእይንቶች (ፖርኖግራፊ)፣ እጾችና አስካሪ መጠጦች፣ የመሳሰሉ መጥፎ ምግባሮች መታቀብ ይኖርብናል፡፡ ድግምት የማድረግ ወይም ሙታንን የማናገር ባዕድ አምልኮ ድርጊት ውስጥ ተሳትፈን ከሆነ፣ እነዚህን ድርጊቶች በፍጥነት ማቆም አለብን፡፡ በዚህም ዙሪያችንን ከአጋንንታዊ ተጽእኖዎች እናጸዳለን፡፡ ከዚያም እግዚአብሔር ይቅር እንዲለንና ውስጣችንን እንዲያጸዳው መጸለይ ይኖርብናል፡፡

ቅደም ተከተል 3:--ሕይወትዎን በብርሐን ይሙሉ፤

የሱስ ክርስቶስ ከጂኒ ኃይል ነጻ ካወጣዎ በኋላ፣ እርሱ የሕይወትዎ ተቆጣጣሪ ይሆን ዘንድ ይጋብዙት፡፡ ልብዎ ባዶ እንደሆን አይተውት፡፡ የሱስ እንዲህ ሲል ተናግሯል፡-

“ርኩስ መንፈስ ከሰው ከወጣ በኋላ ዕረፍት ለማግኘት ውሃ በሌለበት ደረቅ ቦታ ይንከራተታል፤ የሚሻውን ዕረፍት ግን አያገኝም፡፡ ከዚያም ‘ወደ ነበርሁበት ቤት ተመልሼ ልሂድ’ ‘ይላል፤ ሲመለስም ቤቱ ባዶ ሆኖ፣ ጸድቶና ተዘጋጅቶ ያገኘዋል፡፡ ከዚያም ይሄድና ከራሱ የባሱ ሌሎች ሰባት ክፉ መናፍስት ይዞ ይመጣል፤ እነርሱም ሰውየው ውስጥ ገብተው ይኖራሉ፡፡ የዚያም ሰው የኋለኛው ሁኔታ ከፊተኛው የከፋ ይሆናል፡፡” (ማቴዎስ ወንጌል፡ 12፡43-45)፡፡

ከጂኒ ነጻ እንደወጡ፣ ሕይወትዎ የየሱስ ክርስቶስ መጽሐፍ በሆነው በመጽሐፍ ቅዱስ ብርሃን የተሞላ እንዲሆን ያድርጉ፡፡ የሱስ ክርስቶስ እንዲህ ሲል ይናገራል፡ “በእኔ የሚያምን በጨለማ እንዳይኖር ብርሃን ሆኜ ወደ ዓለም መጥቻለሁ” (ዮሐንስ ወንጌል፡ 12፡46)፡፡ የእርሱ ብርሃን ጨለማውን ጠራርጎ ያስወጣው ዘንድ የየሱስን መጽሐፍ ቅጅ ያግኙና በየቀኑ ያንብቡ፡፡

ለወደፊቱ አስተማማኝ ተስፋ መሰነቅ፤

የምንኖረው ርኩሳን መናፍስት ከመቼውም ይልቅ በንቃት በሚሠሩበት እና የዘመኑ መጨረሻ በተቃረበበት ወቅት ላይ ነው፡፡ ከእርሱ ዳግም መገለጥ አስቀድሞ የክፉ ኃይላት አማኞችን ለማሳት በርካታ ሐሰተኛ ታምራቶችን እንደሚያደርጉ የሱስ ክርስቶስ ተንብዮአል፡፡ ለአንዳንዶች ጂኒ የሚያስፈራ ቅርጽ ይዞ የሚገለጥ ሲሆን፣ ለሌሎች ደግሞ እንደ መላእክት ወይም የሞቱ ዘመዶቻቸውን መስሎ ይታያቸዋል፡፡ ዲያብሎስ የሱስ ክርስቶስን የሚመስል ገጽታ እስከ መላበስ በሚደርስ ትዕይንት በሰዎች ፊት ይታያል!

ነገር ግን በሚዘራው ሐሰት መታለል የለቦትም፡፡ የሱስ ክርስቶስን የሚከተሉ ከሆነ፣ ዲያብሎስን ለመቋቋም የሚያስችል ኃይል ይሰጥዎታል፡፡ ዛሬ የቱንም ዓይነት ፈታኝ ሁኔታ ከፊትዎ ሊጋረጥ ቢችል እንኳ፣ የሱስ ክርስቶስ ነጻ ያወጣዎ ዘንድ ይፍቀዱለት!

እርስዎ ከርኩሳን መናፍስት ነጻ ይሆኑ ዘንድ የየሱስ ክርስቶስ ተከታይ እንዲጸልይልዎ የሚፈልጉ ከሆነ፣ እባክዎ ከዚህ ወረቀት ጀርባ ባለው አድራሻ ይጻፉልን፡፡

Copyright © 2023 by Sharing Hope Publications. ለንግድ ዓላማ አይሁን እንጂ ይህንን ፅሑፍ ማሳተምና ማከፋፈል የተፈቀደ ነው፡፡
በዚህ ጽሁፍ ጥቅም ላይ የዋሉት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች የተወሰዱት ከ1993፣ 2003 አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነው፡፡

የዜና መጽሔታችንን ለማግኘት ይመዝገቡ

አዳዲስ ሕትመቶች ሲወጡ ለማወቅ የመጀመሪያ ይሁኑ

newsletter-cover